Our Story [ታሪካችን]
Ihit le Ihitoch was set up organically when the need to support survivors increased over time. Since 2018, the founder Elsabeth (Elsa) has been contacted by different habesha women who had been affected by violence against women, particularly domestic abuse. With the support of her friends, especially Hermela, Tirhas and Wossenyelesh, she used her humble knowledge and experience to provide advice and support. Ihit le Ihitoch Women's Support Group is registered as CIC (Community Interest Company) since October 2025.
Whilst the one-to-one advice and support continues, it was obvious that the group's 'sisters to sisters' support was crucial. Hence, we set up the bi-weekly online women's support group in 2021. The group is a place where members have peer support, knowledge exchange and practical actions including focus group discussions in specific topics. The Advisory board comprised of five women are very dedicated in consulting and participating.
እህት ለእህቶች የሀበሻ ሴቶች ማህበር በሴቶች ደህንነት እና መብት ላይ ባለሙያ የእንግሊዝ አገር ነዋሪ የሆኑ በኢትዮጵያዊ ሴቶች ነው። ከ2018 ጀምሮ የማህበሩ መስራችዋ ኤልሳቤጥ (ኤልሳ) ከባልደረቦችዋ በተለይም ከሄርሜላ፤ ትርሃስ እና ከወሰንየለሽ በምታገኘው ድጋፍ በቤት ውስጥ ጥቃትና በደል የደረሰባቸው ብዙ ሀበሻ ሴቶች ሲቀርብዋት በምታውቀው ትንሽ እውቀት እና በስራ ልምድዋ ምርኩዝ በማድረግ ምክር፣ ድጋፍ፤ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠትዋን ቀጥላለች። ከአንድ ለአንድ እገዛና ድጋፍ በተጨማሪ እህቶቻችን እርስ በርስ መመካከራቸው እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ከ2021 ጀምሮ በየሁለት ሳምንት በዙም እየተገናኘን የተለያዩ ውይይቶችን፤ የተለያዩ ትምህርቶችን፤ እንዲሁም የምክር ስብሰባ ማድረጉን ቀጥለናል:: የአማካሪዎቹ ቦርድ አምስት አባላትን ያቀፈ ሲሆን እነዚህ አባላት የእንቅስቃሴዎቹን እቅድ በማውጣትና በስብሰባዎቹ ላይ በመሳተፍ የተጉ ናቸው።
Our Expertise [ልዩ ሙያችን]
Ihit le Ihitoch Habesha Women's Group was formed by Ethiopian women professionals for Ethiopian and Eritrean women based in the UK but we provide awareness-raising sessions to our sisters globally. We have a combined experience of twenty years of working in the VAWG sector both in the UK and Sub-Saharan Africa. The directors have a track record of providing quality advice and support for their fellow women voluntarily. Ihit le Ihitoch Habesha Women's Support Group members who are survivors of VAWG continue to support each other and refer their sisters for help to the group.
እህት ለእህቶች የሀበሻ ሴቶች መረዳጃ ማህበር የተቋቋመው በሴቶች ጉዳይ ዘርፍ ላይ ለብዙ አመታት ያገለገሉ ሴቶች በበጎ ፈቃደኝነት እህቶቻቸውን ለማገዝ የተቋቋመ ነው። ከዛም በተጨማሪ በአለም አቀፍ ለሚገኙ እህቶቻችን ስለሴቶች ጥቃት እውቀት የሚያሳድጉ ስልጠናዎች እናቀርባለን። አደራጆቹ በአጠቃላይ ከሀያ አመታት በላይ ልምድ አላቸው ስለዚህም ጥሩና ውጤታማ የሆነ ምክርና አገልግሎት መስጠታቸውን ቀጥለዋል። የማህበሩ አባላቶች እርስ በርስ መረዳዳት እና ሎሎች እገዛ የሚያስፈልጋቸውን እህቶቻችንን ወደ ማህበሩ በማምጣት ይተጋሉ።