Our Values [መሰረታዊ እሴቶቻችን]
Sisterhood: We are more than a group - we are sisters. Together we build trust, care deeply for one another, and create a place where everyone feels valued and included.
እኅትማማችነት: እኛ ከማህበር በላይ ነን — እኛ እኅትማማች ነን። በአንድነት እምነትን እንገንባ፤ እርስ በርሳችን በጥልቅ እንተጋገዛለን፤ እያንዳንዳችን የምንከበርበት እንደተካተትን የሚሰማን ቦታ እንፈጥራለን።
Compassion: We support each other through joy and pain, offering kindness, empathy, and genuine care without judgment.
ርኅራኄ: በደስታና በህመም ጊዜ እርስ በርሳችን እንደጋገፋለን፤ እራሳችንን በእህታችን ቦታ በማስቀመጥ ያላንዳች አድሎ እና ፍርድ እርዳታ እና እውነተኛ እንክብካቤ እናቀርባለን፡፡
Safety: We create a space where women can speak freely, share their stories, and find comfort knowing they are understood, believed, and protected.
ደህንነት: ሴቶች በነፃ እንዲያወሩ፣ ታሪካቸውን እንዲያጋሩ፣ስሜታቸው እንደሚረዳ እና እንደሚጠበቅ ፤እንደሚታመኑ በማወቅ ደህንነት እና ማረፊያ የሚሰጥ ቦታ እንፈጥራለን።
Hope: We help each other find strength in difficult times, inspiring confidence, healing, and belief in a brighter future.
ተስፋ: በአስቸጋሪ ጊዜዎች ውስጥ ጥንካሬን እንንዲያጎለብቱ እርስ በርሳችን እንረዳዳለን፤ መተማመን፣ የስሜት ቀውስ ማገገሚያ እና በብርሃናማ ወደፊት ላይ እምነትን እንነሳሳለን።
Growth: We grow together - learning about life, wellbeing, parenting, domestic abuse, and the systems around us - building knowledge that leads to freedom and resilience.
እድገት: እኛ በአንድነት እናድጋለን — ስለ ሕይወት፣ ጤና እና ደህንነት፣ ልጆችን ስለማሳደግ፣ በሴቶች ላይ የሚደርሱ አመጽ እና የቤት ውስጥ ጥቃት እንዲሁም በዙሪያችን ያሉ ስርዓቶች እየተማርን — ነፃነትና እርግጠኝነት የሚያመጣ እውቀትን እንገንባለን።
Generosity: When one sister rises, she lifts others with her. We share what we know, help where we can, and build a community that gives back.
ልግስና: አንዲት እኅታችን ስትነሳ፤ ሌሎችን ከእርሷ ጋር ታነሳለች። የምናውቀውን እንካፍላለን፤ በምንችለው እንረዳዳለን፤ መልሶ የሚሰጥ ማህበረሰብን እንገንባለን።
Our Approach [አሰራራችን]
At Ihit le Ihitoch Habesha Women's Support Group, we believe that the voices of our members - who are survivors of VAWG, particularly domestic abuse - are at the centre of our mission. We work closely with each member to understand her unique needs and goals, and provide personalised advice and support. We also work closely with partner organisations, IDVAs and support workers who provide support to our members to improve the quality of service provided to them.
እህት ለእህቶች መረዳጃ ማህበር ማንኛውንም ውሳኔ የአባላቶቹን በተለይም የቤት ውስጥ ጥቃት ተሞክሮ ያላቸውን ሴቶች ድምፅ ማጉላት እና የነሱን ሀሳብና ፍላጎት መሰርት በማደረግ ይወስናል። ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋርም በመተባበር ለአባላቶቹ የሚያስፈልጋቸውን እገዛ ያቀርባል። ከአጋዥ ድርጅቶች ጋርም ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ለአባሎቻችን የተመቻቸ ሁኔታ እንዲያገኝ እናደርጋለን።